✅ በሽልማት የተበረከተለቴን መሬት በመሸጥ ለሚወደው እግር ኳስ ያበረከተ አሰልጣኝ።
መኮነን ገላነህ (ዊሀ) ማነው ?
👉 ይህ አሰልጣኝ በተጫዋችነትም በአሰልጣኝነቱም የተሳካለት ነበር።
ይህ ሰው የአርባምንጭ ከተማ ፍሬ የህነው #መኮነን_ገላነህ በቅፅል ሱሙ #ዊሀ ይባላል ።
እግር ኳስን በተጫዋችነት 1989 አም እስከ 2001 አም ተጫውቶ ያለፈ ሲሆን በተጫዋችነት ጊዜው በታላላቅ ክለቦች አገልግሎት ሲሰጥ የተጫወተባቸው ክለቦች ደግሞ ከታች ተዘርዝረዋል።
👇 በክለብ ደረጃ የተጫወተባቸው ቡድኖች
✅ ሀዋሳ ከተማ
✅ አርባምንጭ ጨርቃ ጨርቅ
✅ ወንጂ ስኳር
✅ ሐረር ቢራ
✅ አዳማ ከተማ
✅ ኦሜድላና
✅ ሻሸመኔ ከተማ ለ 13 አመታት መጫወት የቻለ ሲሆን ለብሄራዊ ቡድን ደግሞ በተለያዩ የእድሜ እርከኖች ተጫውቷል።
✅ ከ 17 አመት በታች
✅ ከ 20 አመት በታች
✅ ከ 23 አመት በታች ለኦሎምፒክ እና ለዋናው ብሄራዊ ቡድን አገልግሏል።
✍ በተጫዋችነት ስኬታማ ጊዜን ያሳለፈው ይህ አሰልጣኝ ከተጫዋችነት ወደ አሰልጣኝነት በመግባት ያለው የጠለቀና የረዥም ጊዜ የጫዋታ ልምድ ለማካፈል ቆርጦ በመነሳት በ 2002 አም #Weax 95 እግር ኳስ ፕሮጀክት በአርባምንጭ ከተማ ማቋቋም ችሏል።
ከዛም አልፎ በእግር ኳስ ተጫዋችነቱ የሰበሰባቸውን ገንዘብ ላቋቋመው ፕሮጀክት የተለያዩ የስፖርት ቁሳቁስ ግዢ አውሏል።
ያቋቋመው ፕሮጀክት ከ 15 አመት በታች ሲሆን በወንድ 30 በሴቶች 30 ባጠቃላይ 60 ሰልጣኞች በፕሮጀክቱ አቅፎ ማሰራት ችሏል። በዚህ ጉዞላይ ግን መሀል ላይ የፋይናንስ እጥረት ገጠመው እሰከ አሁን ከራሱ ያለውን ብር ተጠቅሞ ተጉዞ ነበር አሰልጣኞቹ የስፖርት ቁሳቁስ በመጨረሳቸው ይህ አሰልጣኝ ከባድ ውሳኔ ወሰነ ። የጀመረውን ፕሮጀክት እንዳይቆምና እንዳይፈርስ በማሰብ በተጫዋችነት ወቅት ለ አርባምንጭ ጨርቃጨርቅ ቡድን ባረገው ተሳትፎና ባገኘው ዋንጫ ምክንያት በጋሞ ዞን አስተዳደር አማካኝነት በ አርባምንጭ ከተማ በሽልማት መልክ የተበረከተለትን መሬት በመሸጥ ለፕሮጀክቱ በማዋል ያሰበውን ምኞት በማስቀጠል በርካታ ታዳጊዎች ለሀገር አብቅቷል። በዚህ ፕሮጀክት 6 የውጣ ውረድ አመታት በማሳለፍ የልፋቱን ፍሬ ማየት ሲችል እስከ 2008 የ Weax 95 ፕሮጀክት ውጤት የሆኑት ከብዙ በጥቂቱ ለአብነት ያክል ከታች የተዘረዘሩት ተጫዋቾች ማለትም
✅ ይሳቅ ተገኝና
✅ በላይ ገዛኸኝ ለአርባምንጭ ከተማ ሳበቃ
✅ አረጋሽ ካሳና
✅ ቤቴሊሔም ታምሩ ደግሞ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ለብሄራዊ ቡድኑ ተመርጠው ተጫውተዋል።
👉 በ 2008 አም በመላው ኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ውድድር ላይ የደቡብ ክልል የሴቶች እግር ኳስ በአሰልጣኝነት በመያዝ 3ኛ ደረጃ በማስያዝ የነሐስ ሜዳልያ ተሸላሚ መሆን ችሏል።
✍ ከክልል ውድድር መልስ በክለብ ደረጃ በሁለተኛ ዙር ለመጀመሪያ ጊዜ ጎፋ ባሬንቼን በአሰልጣኝነት በመረከብ መልካም የሚባል አመት ከጥሩ እንቅስቃሴ ጋር የተሻለ ቡድን መስራት ችሏል።
✍ በ 2009 አም ሀምባሪቾን በምክትል አሰልጣኝነት በመያዝ ክለቡን ወደ ከፍተኛ ሊግ ማሳደግ ችሏል።
✍ በ 2010 አም ቀጥታ ወደ ባህርዳር በማቅናት የማንጎ ምክትል በመሆን ባህርዳር ከተማ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማሳደግ ችሏል።
✍ በ 2011 አም ሀላባ ከተማን በምክትል አሰልጣኝነት የሰራ ሲሆን በሀላማ አመቱን ከጨረሰ ቡሀላ በቀጥታ ወደ የመጀመሪያው ክለብ ወደ ሆነው ጎፋ ባሬንቼን በ 2012 አም ተቀላቅሏል። በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ለሚሳተፈው ክለብ ክለብ በምድቡ ውብ የሆነ ማራኪ እንቅስቃሴ የሚጫወት ቡድን የሰራ ሲሆን ቡድኑ በምድቡ የተሻለ ውጤት በማምጣት በ 2013 አም በአዳማ ከተማ በተከናወነው የአንደኛ ሊግ ማጠቃለያ ውድድር አልፎ በውድድሩ ክስተት የሆነ ክለብ የሰራ ሲሆን በአጨዋወቱ ረገድ ለተመልካች ቀልብ የሚስብ አጨዋወት በመጠቅም አዳማ ለተገኘው የእግር ኳስ ተከታይ ያስደመመ ጫዋታ በማሳየት ወደ ከፍተኛ ሊግ ለማለፍ ጫፍ ደርሶ ስምንት ውስጥ ገብቶ ውድድሩን ማገባደድ ችሏል።
✅ አሰልጣኝ መኮነን ገላነህ #ዊሀ ተወልዶ ያደገው በ ውቢቷ የፍቅር ከተማ አርባምንጭ ሲሆን በወቅቱ በነበረው የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ለተለያዩ ክለቦች በተጫዋችነት ማገልገል ችሏል። ይህ ሰው ወደ አሰልጣኝነት በክለብ ደረጃ የተቀላቀለው በ2008 አም ሲሆን ክለቡም በጥንካሬው የሚታወቀው በአንደኛ ሊጉ ድምቀት ከነበሩ አንዱ የደቡቡ ክለብ ለጎፋ ባሬንቼ እግር ኳስ ክለብ በዋና አሰልጣኝነት ለአንድ አመት ማገልገል ችሏል።
❓2014/15 አም የውድድር አመት መኮነን ገላነህ #ዊሀ የት እንመልከተው ይሆን?
✅ ታላቁ አሰልጣኝ ወደ ታችኛው ሊግ ወርዶ ተፈትኖ አልፏል።
👍 ስለዚህ ጥበበኛ አሰልጣኝ ከብዙ በጥቂቱ እንዲህ አልናቹህ። 🎙 #ዳጉ_ስፖርት የኢትዮጵያ ታችኛው ሊግ ብቸኛዋ ድምፅ