
✍ በሳልሀዲን ሰይድ ታላቅ ወንድም በዋና አሰልጣኝነት የሚመራው ክለብ በፋይናንስ እጥረት በሊጉ የመሳተፉ ጉዳይ አጠራጣሪ ሁኗል።
✅ በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ምድብ ሐ ተደልድሎ በአንደኛው ዙር አሰላ ከተማ በተደረገው ውድድር የምድቡ አራተኛ ደሠጃን ይዞ ዙሩን ያጠናቀቀው የቤንሻንጉል ክልል ተወካይ አሶሳ ከተማ ባሁኑ ሰአት በሁለተኛ ዙሩ የመሳተፉ ጉዳይ በገጠመው የፋይናንስ እጥረት አጠራጣሪ እንደሆነ ለክለቡ ቅርበት ካላቸው አካላት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ታሪካዊ ተጫዋች የሰልሀዲ ሰይድ ወንድም አረፋት ሰይድ የሚመራው በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ምድብ ሐ ተደልድሎ አንደኛ ዙሩን በአሰላ ከተማ ተጫውቶ በጥሩ ውጤት ያጠናቀቀው አሶሳ ከተማ በምድቡ አስር ጫዋታ በማከናወን አራት ጫዋታ አሸንፎ በሶስቱ ነጥብ ተጋርቶ በሶስት ጫዋታ በመረታት ባጠቃላይ 15 ነጥቦችን በመሰብሰብ የምድቡ መሪ ከሆነው አረካ ከተማ በአራት ነጥብ ተበልጦ አራተኛ ደረጃ ላይ በመሆን ሲያጠናቅቅ በመሆኑም አሰላ ከተማ በነበረው ውድድር ነገሮች አልጋ ባልጋ አልነበሩም በበርካታ ችግሮች አልፎ ውድድሩን በጥሩ ውጤትና ደረጃ ዙሩን ማጠናቀቅ ችሏል።
ይህ ጠንካራ ክለብ ሁለተኛ ዙሩ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 19/2017 ዓም መሆኑ እየታወቀ እስከ አሁን ወደ ዝግጅት አለመግባቱ የብዙ የክልሉ ስፖርት ወዳድ ማህበረሰብ ድንጋጤን ፈጥሯል።
በክለቡ የሚጫወቱ ተጫዋቾች የሶስት ወር ደመወዝ አለመከፈላቸው ለዳጉ ስፖርት የደረሰው መረጃ ያመላክታል ።
✅ የክለቡ ቅርበት ካለው አንድ የመረጃ ምንጫችን ለማረጋግጥ እንደቻልነው ክለቡ አንደኛ ዙሩን አሰላ ከተማ በተደረገበት ሰአት ለተጫዋቾቹ ሙሉ ወጭ ሸፍኖ ውድድሩ እንዲጨርሱ ያረገው የክለቡ አሰልጣኝ የሆነው አረፋት ሰይድ አማካኝነት ነው በማለት ሲገልፁ ከዛ በተጨማሪ ክለቡ ትጥቅ ሳይገዛለት ለዚህ ውጤት እንደደረሱ የሶስት ወር ደመወዝ ለቡድኑ ልኡካን አለመከፈሉ አክለው የገለፁ ሲሆን ክለቡ ባሁኑ ሰአት ለሁለተኛ ዙር ቡራዩ ከተማ ለሚደረገው ውድድር እስከ አሁን ለተጫዋቾች ጥሪ አለመደረጉ ጨምረው ገልፀውልናል።
አሶሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለምን ወደ ዝግጅት እንዳልተመለሰ የሚመለከተው አካላትን አናግረን ምላሹን ለማቅረብ እንሞክራለን ።
©️ ዳጉ Sport by Nuru Kadaba