
✍ የ 2014 ዓም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 2ኛ ዙር ዛሬ ሲጀምር የምድብ ሐ ውድድር በሀዋሳ ከተማ በሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታድዬም ዛሬ የካቲት 12/2014 ዓም ተጀምሯል ።
✅ በምድብ ሐ በሀዋሳ ከተማ በመገኘት የመክፈቻ ጫዋታውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚና የከፍተኛ ሊግ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አሊሚራህ መሀመድ እና የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ አንበሴ እና ሌሎች የክብር እንግድነት በተገኙበት የጅማ አባ ቡና እና ፌደራል ፖሊስ ጫዋታ ሜዳ በመገኘት አስጀምረውታል።


✅ በመክፈቻው ጫዋታ ጅማ አባ ቡና እና ፌደራል ፖሊስ ባገናኘው ጫዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ተጠናቋል። በጫዋታው ፖሊሶቹ ሁለት ያለቀላቸው ኳሶችን አግንተው ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል በተለይ በጫዋታው ፌደራል ፖሊሶች ያገኙት ፔናሊቲ በጅማ አባ ቡና በረኛ በሚገርም ብቃት አድኖባቸዋል።



✍ ዳጉ ስፖርት በተለያዩ ስታድዬም ላይ በመገኘት ጫዋታዎቹን እየዘገብን እንገኛለን። T.me/Dagu_Sport