የኢትዮጵያ ወንዶች ከፍተኛ ሊግ የምድብ ሀ ቅድመ ጫዋታ ዳሰሳ

🇪🇹 #የኢትዮጵያወንዶችከፍተኛ_ሊግ 🇪🇹

✍ የኢትዮጵያ ወንዶች ከፍተኛ ሊግ ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 12/2014 ዓም የ 2ኛ ዙር ጫዋታዎች በሶስቱ ምድቦች የተጀመሩ ሲሆኑ የ 10ኛ ጫዋታ የመጀመሪያ ቀን መርሀግብሮች ሲደረጉ የሁለተኛ ቀን ውሎ ነገ በሚደረጉ ጫዋታ ቀጥሎ ይውላሉ።

✅ የምድብ ሀ 10ኛ ጫዋታ ነገ እሁድ የካቲት 13/2014 ዓም ሁለት ጫዋታዎች የሚከናወኑ ይሆናል።
1⃣. ቀድሞ 8:00 ሰአት ላይ ጌድኦ ዲላ ከ ሀላባ ከተማ የሚጫወቱ ይሆናል። ሁለቱም ቡድኖች በአንደኛው ዙር አንድ ጊዜ ሲገናኙ በጫዋታው ጌዲኦ ዲላ ተጋጣሚውን ሀላባ ከተማን ሁለት ለአንድ በማሸኘፍ ሶስት ነጥብ ማግኘቱ አይዘነጋም። አሁን ለሁለተኛ ጊዜ በሚገናኙበት ወሳኝ ጫዋታ ውጤቱ ለሁለቱም ትልቅ ትርጉም የሚሰጥ ሲሆን አንዳቸው ካንዳቸው ተሸናንፈው ከወራጅ ቀጠናው የሚወጡበት ወሳኝ ተጠባቂ ጫዋታ ከወዲሁ ይጠበቃል።

👉 10ኛ ሳምንት ጫዋታ
8:00/ ጌዲኦ ዲላ 🆚 ሀላባ ከተማ
👉 1ኛ ሳምንት ላይ ሲገናኙ
ሀላባ ከተማ 1-2 ጌድኦ ዲላ

⏳ #የክለቦችቁጥራዊመረጃ ⏳
⏳ #ምድብጫዋታቁጥራዊ_መረጃ ⏳

ጌዲ ኦዲላ 🆚 ሀላባ ከተማ

9 ተጫወተ 9

2 አሸነፈ 2

3 አቻ 2

4 ተሸነፈ 5

34% አሸናፊነት 30%

6 አስቆጠረ 7

10 ተቆጠረበት 11

0.67 አስ.ጎል/ጫዋታ 0.78


1.1 ተቆ.ጎል/ጫዋታ 1.2


9 ነጥብ 8


8 ደረጃ 9


3 ነጥብ እርስበርስ 0

✅ የሁለቱም ቡድኖች ቁጥራዊ መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ በማጥቃቱ በኩል ሀላባ ከተማ የተሻሉ ሲሆኑ በመከላከሉ ረገድ ደግሞ ጌድኦ ዲላ የተሻለ ሲሆን እርስ በርስ በተገናኙበት ጫዋታ ጌድኦ ዲላ የተሻለ ቁጥራዊ ብልጫ ወስዷል።

2⃣. በመቀጠል 10:00 ሰአት ላይ የሳምንቱ የመጨረሻው ጫዋታ በባቱ ከተማ እና ሻሸመኔ ከተማ መካከል የሚደረግ ሲሆን ሁለቱም ቡድኖች በአንደኛው ዙር አንድ ጊዜ ሲገናኙ በጫዋታው ባቱ ከተማ ተጋጣሚውን ሻሸመኔ ከተማን አንድ ለምንም በማሸኘፍ ሶስት ነጥብ ማግኘቱ አይዘነጋም። አሁን ለሁለተኛ ጊዜ በሚገናኙበት ወሳኝ ጫዋታ ባቱዎች ይህንን ጫዋታ ማሸነፍ ከቻሉ ከመሪዎቹ ጋር ያላቸው የነጥብ ልዩነት ከ 11 ወደ 8 የሚያጠቡበት ሲሆን ተጋጣሚው ሻሸመኔ ከተማ በበኩሉ ጫዋታው በመርታት ከወራጅ ቀጠናው እራሳቸውን የሚያርቁበት ደረጃቸውን ከፍ የሚያደርጉበት ሊሆን ይችላል።

👉 10ኛ ሳምንት ጫዋታ
10:00/ ባቱ ከተማ 🆚 ሻሸመኔ ከተማ
👉 1ኛ ሳምንት ላይ ሲገናኙ
ሻሸመኔ ከተማ 0-1 ባቱ ከተማ

⏳ #ምድብጫዋታቁጥራዊ_መረጃ ⏳

ባቱ ከተማ 🆚 ሻሸመኔ ከተማ

9 ተጫወተ 9

2 አሸነፈ 3

6 አቻ 1

1 ተሸነፈ 5

45% አሸናፊነት 37%

8 አስቆጠረ 8

5 ተቆጠረበት 11

0.89 አስ.ጎል/ጫዋታ 0.89


0.56 ተቆ.ጎል/ጫዋታ 1.2


12 ነጥብ 10


5 ደረጃ 7


3 ነጥብ እርስበርስ 0

✅ የሁለቱም ቡድኖች ቁጥራዊ መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ በማጥቃቱ በኩል ተመሳሳይ ሲሆኑ በመከላከሉ ረገድ ደግሞ ባቱ ከተማ የተሻለ ሲሆን እርስ በርስ በተገናኙበት ጫዋታ ባቱ ከተማ የተሻለ ቁጥራዊ ብልጫ ወስዷል።

©️ ዳጉ Sport by Nuru Kadaba

Leave a comment

Design a site like this with WordPress.com
Get started