
🇪🇹Betking Ethio Premier League🇪🇹
✍ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጫዋታዎች ተጠናቋል።
✅ መሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ጥሏል። ሐሙስ የካቲት 10/2014 አም መሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀድያ ሆሳዕናን ገጥሞ ያለምንም ግብ አቻ የወጡ ሲሆን የነጥብ ልዩነቱን ማስፋት ሳይችል ቀርቷል።
✅ የአምናው ሻምፕዮን አፄዎቹ ወጥ አቋም ማሳየት ተስኗቸዋል። የሳምቱ ተጠባቂ የነበረው ጫዋታ ማክሰኞ የካቲት 8/2014 አም የአምናው ሻምፕዮና ፋሲል ከነማ ከ ሀዋሳ ከተማ ያገናኘ ሲሆን ከጫዋታ ጫዋታ ጥንካሬውን እያሳዩ የመጡት ሀዋሳዎች ጫዋታውን ሁለት ለአንድ በማሸነፍ ግስጋሴያቸውን ሲቀጥሉ ተሸናፊው ፋሲል በበኩሉ ከነበረበት ደረጃ እየተንሸራተተ ይገኛል። ሀዋሳ ከተማ ይህንን ተጠባቂ ጫዋታ በድል በመወጣቱ በ23 ነጥቦች በደረጃ ሠንጠረዡ ሁለተኛ ደረጃ የተቀመጡ ሲሆን ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ የነበራቸው የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ማጥበብ ችለዋል።
✅ አዲስ አበባ ከተማ በጎል የተንበሸበሸበት ድል ተቀዳጅቷል። ሁለቱም በወራጅ ቀጠና የሚገኙት ክለቦችን ያፐናኘ ማክሰኞ የካቲት 8/2014 አም ሰበታ ከተማ ከአዲስ አበባ ከተማ ያገናኘው ጫዋታ በአዲስ አበባ ከተማ ፍፁም የበላይነት ተጋጣምያቸውን አምስት ለአንድ በማሸነፍ በጎል የተንበሸበሹበት ድል ያስመዘገቡ ሲሆን በሳምንቱ ከተደረጉት ጫዋታዎች ከፍተኛ ግብ ያስተናገደ ጫዋታ ሁኖ አልፏል። አዲስ አበባ ከተማዎች ይህንን ጫዋታ በማሸነፋቸው ከወራጅ ቀጠናው ባይወጡም ከ13ኛ ከተቀመጠው ድሬዳዋ ከተማ የነበራቸው የአራት ነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት በማጥበብ ከወራጅ ቀጠናው የሚወጡበት መንገድ ላይ ይገኛሉ። ተሸናፊው ሰበታ ከተማ በወራጅ ቀጠናው ሲቀጥል የደረጃ ግርጌ ላይ ተቀምጧል።
✅ አርባምንጭ ከተማ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ሲያገኝ የሸገሩ ቡና ተሸንፏል። ቀድሞ የብዙዎች ስፖርት ወዳድ ቀልብ የሳበው ጫዋታ ረቡዕ የካቲት 9/2014 አም በአዞዎቹና በሸገር ቡናዎቹ ጋር የተደረገው ጫዋታ በአዞዎቹ አንድ ለምንም አሸናፊነት ሲጠናቀቅ ባለ ድሉ አርባምንጭ ከተማ ከወራጅ ቀጠናው ያስወጣው ጣፋጭ ሶስት ነጥብ ሲያገኝ የሸገሩ ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ ወደ መሪዎች የሚጠጋበት እድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
✅ ወደ ውጤታማነት ገብቶ የነበረው አዳማ ከተማ በጦሮቹ ሽንፈት ደረሰበት። ከጫዋታ ጫዋታ እየተሻሻለ የመጣው አዳማ ከተማ ሐሙስ የካቲት 10/2014 አም መከላከያን ገጥሞ አንድ ለምንም በመከላከያ ተሸንፏል ።
✅ ወላይታ ድቻ ወደ መሪው የሚጠጋበትን እድል አመከነ። ወራጅ ቀጠናው ላይ የሚገኘው ጅማ አባ ጅፋርን አርብ የካቲት 11/2014 አም የገጠመው ወላይታ ድቻ በጅማ አባ ጅፋር አንድ ለምንም ሲሸነፍ ባለ ድሉ ጅማ አባ ጅፋር በሊጉ ሶስተኛ ድሉን አስመዝግቧል ። ተሸናፊው ወላይታ ድቻ በበኩሉ ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ የነበረው የነጥብ ልዩነት ማጥበብ ሳይችል ሲቀር መሸነፉን ተከትሎ ከነበረበት ደረጃ በመውረድ በ22 ነጥቦች አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
✅ ድሬዳዋ ከተማ ከ ባህርዳር ከተማ ና ሲዳማ ቡና ከ ወልቂጤ ከተማ በተመሳሳይ ያለግብ አቻ የተጠናቀቀ ጫዋታ ነው።
©️ ዳጉ Sport by Nuru Kadaba