በዶክተር ጃዕፈር ያሲን ባለቤትነት የሚመራው በጅማ ከተማ የሚገኘው ኦዳ ሁሌ ሆስፒታል እግር ኳስ_ክለብ በኦሮምያ ሊግ ጥሩ እንቅስቃሴ ካሳዩት ጥቂት ክለቦች አንዱ ነው።

ኦዳ ሁሌ ሆስፒታል እግር ኮስ ክለብ

✅ በዶክተር ጃዕፈር ያሲን ባለቤትነት የሚመራው በጅማ ከተማ የሚገኘው #ኦዳሁሌሆስፒታልእግርኳስ_ክለብ በኦሮምያ ሊግ ጥሩ እንቅስቃሴ ካሳዩት ጥቂት ክለቦች አንዱ ነው።

በዶክተር ጃዕፈር የሚመራው ኦዳ ሁሌ

ኦሮሚያ ሊግ ውድድር 70 ክለቦችን በ 7 ምድቦች ተከፍሎ የሚካሆድ ሲሆን
ከምድብ ከ 1-3 የወጡት በቀጥታ የሚያልፉ ይሆናል በተጨማርም 3 ክለቦች ጥሩ 4ተኛ የሆኑት በማለፍ
በ 24 ክለቦች መሀከል የመጨረሻው የጥሎ ማለፍ ውድድር ይካሄዳል። በዚህ ውድድር ደግሞ ከምድብ አንድ ከተደለደሉት ውስጥ አንዱ የዶክተር ጃዕፈር ኦዳ ሁሌ ሆስፒታል እግር ኳስ ክለብ አንዱ ነው። ይህ ክለብ ምድቡን በሶስተኝነት መጨረስ ችሏል።

✅ ክለቡ 2004 ከታዳጊ ፕሮጀክት ጀምሮ የተመሰረተ ሲሆን በ2010 የኦሮሚያ ክለቦች ሻፕዮና ላይ በመሳተፋ ወደ ኦሮሚያ ሊግ መግባት ችሏል። ኦሮሚያ ሊግ ላይ ከ 2011 ጀምሮ እስካሁን 4 አመት መወዳደር የቻለ ሲሆን ከፕሮጀክት ጀምሮ ኦሮሚያ ሊግ 3 አመት ሙሉ ሲወዳደር ጅማ ሸነን ጊቤ በመባል ነበር የሚጠራው በዚህ በያዝነው አመት 2014 አም የኦዳ ሁሌ ሆስፒታል ባለቤት ዶክተር ጃዕፈር ተመልክተው ክለቡን ሙሉ በሙሉ ስያሜውን በማስቀየር በዚህ የውድድር አመት በርካቲ ፋይናንስ ወጪ በማድረግ ክለቡን ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ ችለዋል።
እስካሁን በዚ ክለብ ውስጥ የለፉ ከ15 የሚበልጡ ልጆች ከፍተኛ ሊግ እና ቤራዊ ሊግ የተወሰኑ ልጆች ኘርሚየር ሊግም መድረስ ችለዋል።

ኦዳ ሁሌ እግር ኳስ ክለብ

✍ ይህ ክለብ በሀገራችን ከሚገኙት ጥቂት የግል ክለቦች መሀከል አንዱ ሲሆን ኦዳ ሁሌ ሆስፒታል ለብዙ የሀገራችን ድርጅቶች አራአያ በመሆን ብቅ ብሏል ።
ኦዳ ሁሌ ሆስፒታል በጅማ ከተማ ውስጥ ይገኛል ይህ ሆስፒታልም የራሱ የሆነ የእግር ኳስ ክለብ ይዟል ።
ኦዳ ሁሌ ሆስፒታል እግር ኳስ ክለብ በዘድሮው አመት በኦሮሚያ ሊግ ምድብ A ላይ ተደልድሎ የተወዳደረ ሲሆን ምድብ A የኦሮሚያ ሊግ ውድድር በ8 ክለቦች በጅማ ከተማ አስተናጋጅነት የተካሆደ ሲሆን በውድድሩ ላይም ኦዳ ሁሌ ሆስፒታል እግር ኳስ ክለብ 7 ጫዋታ አከናውኖ 4 ጫዋታ ድል ሲቀናው በሁለት ጫዋታ አቻ ተለያይቶ በቀሪው አንድ ጫዊታ ተሸንፎ በተጋጣሚዎቹ 14 ጎሎችን በማስቆጠር በአንፃሩ 11 ግቦች ተቆጥረውበት 14 ነጥቦችን በመሰብሰብ በ 3ኛ ደረጃ በማጠናቀቅ ለመጨረሻው ኦሮሚያ ሊግ የጥሎማለፍ ውድድር ማለፉን አረጋግጧል ።

ኦዳ ሁሌ ምድቡን በሶስተኝነት ጨርሷል

©️ ዳጉ Sport by Nuru Kadaba

Leave a comment

Design a site like this with WordPress.com
Get started