✍ በቀድሞው ሆላንዳዊው የሊቨርፑል ኮከብ ሪያን ባብል ስም የሚጠራው የፊት መስመር ሮኬቱ ኮከብ ምትኩ ጌታቸው ማነው ?

✍ ይህ በ #ነጌሌ_አርሲ ውስጥ እየተጫወተ የሚገኘው ክለቡ በምድቡ አንደኛ ዙር ላይ ሁለተኛ ሁኖ እንዲጨርስ ትልቅ ሚና ከተጫወቱት መሀል ስሙ የሚገኘው የፊት መስመሩ ሮኬ ባብል ጋር ዳጉ Sport ቆይታ አርጋለች ሙሉ ቃለ ምልልስ ሰፋ ባለ ፅሁፍ ይዘን እንቀርባለን ይጠብቁን።
✍ ተወልዶ ያደገው በነገሌ አርሲ ከተማ ሲሆን በኢትዮጵያ ሊግ ደረጃ ሰባት አመታት መጫወት የቻለ ሲሆን በተጫወተባቸው ክለቦች ባጠቃላይ ከመስመር እየተነሳ 31 ጎሎችን በማስቆጠር የተሻለ ጨራሽ አጥቂ መህኑን ያሳየ ሲሆን በየአመቱ በተጫወተባቸው ቡድኖች ከፍተኛ ግብ አግቢነት ተፎካካሪ መሆን የቻለ በዚህ ሲዝን ለነገሌ አርሲ ሰባት ጫዋታ በማድረግ አራት ጎሎችን ማስቆጠር የቻለ ታታሪ ተጫዋች ነው።
እስከ አሁን የተጫወተባቸው ክለቦች አራት ናቸው።
✅ ነጌሌ አርሲ
✅ ጌዲኦ ዲላ
✅ ቡታጀራ ከተማ
✅ ሻሸመኔ ከተማ በነዚህ ክለቦች ይህ ኮከብ ያረገው አስተዋፆ ምን ነበር ከዳጉ ስፖርት ጋር ያረገው ቃለመጠይቅ ይከታተሉ።
ዳጉ Sport :- የምትጫወትበት እውነተኛ ቦታ የቱጋ ነው?
ምትኩ (ባብል) :- የመስመር አጥቂ
ዳጉ Sport :- በ2014 ለነገሌ አርሲ በአንደኛው ዙር ላይ እስከ አሁን ስንት ጎሎች አስቆጥረሀል ?
በስንት ጫዋታ ተሳተፍክ ?
ምትኩ (ባብል) :- ለነገሌ ሰባት ጫዋታ ተጫውቼ አራት ጎሎችን አስቆጥሬያለሁ
ዳጉ Sport :- በሊግ ደረጃ ለተጫወትክባቸው ክለቦች ስንት ግብ አስቆጥረሀል ?
ምትኩ (ባብል) :- 31 ጎሎች ማስቆጠር ችያለሁ
በ2010 ለቡታጅራ ከተማ 5 ጎሎች
በ2011 ለነገሌ አርሲ ከተማ 11 ጎሎች
በ2012 ለጌድኦ ዲላ በኮቪድ እስከተቋረጠበት ድረስ 3 ጎሎችን አግብቻለሁ
በ2013 ለነገሌ አርሲ 8 ጎሎች
በ2014 ለነገሌ አርሲ በአንደኛው ዙር 4 ጎሎችን ማስቆጠር ችያለሁ።
ዳጉ Sport :- ተጫዋች እንድትሆን አርአያ የሆንህ ማነው ?
ምትኩ (ምትኩ) :- ሪያን ባብል
ዳጉ Sport :- ላንተ በዚህ ደረጃ መገኘት ትልቁን ድርሻ የሚወስደው ማነው ?
ምትኩ (ባብል) :- ሁሌ ከጎኔ በመሆን ትልቅ ድጋፍ የሚሰጡኝ ደጋፊዎቼ ፣ ቤተሰቦቼና የቡድን አጋሮቼ
ዳጉ Sport :- ከሀገር ውስጥ ተጫዋቾች የማን አድናቂ ነህ ?
ምትኩ (ባብል) :- ጌታነህ ከበደና ሙሉቀን አዲሱ ናቸው
ዳጉ Sport :- ሙሉቀን አዲሱ ለማን ቡድን የሚጫወት ነው ? የሚጫወትበት ቦታስ ?
ምትኩ (ባብል) :- ሙሉቀን አዲሱ ለአዲስ አበባ ከተማ እየተጫወተ የሚገኝ ስኪመር ነው።
ዳጉ Sport :- ከውጭስ ማንን ነው የምታደንቀው?
ምትኩ (ባብል) :- የአለማችን ኮከቡ ክሪስትኖ ሮናልዶን ነው
ዳጉ Sport :- ነገሌ አርሲ አሁን እያሳየ ያለው ጠንካራ ግስጋሴ መድረሱ ሚስጥሩ ምንድነው?
ምትኩ (ባብል) :- አንድነታችን ነው ቡድኑ የማሸነፍ ተነሳሽነቱ ከፍ ያለ ሲሆን እርስበራሳችን እንደ አንድ ሁነን በመቅረባችን ነው ለዚህ ያበቃን።
ዳጉ Sport :- የቀጣይ አመት እቅድህስ ምንድን ነው በነገሌ አርሲ ትቀጥላለህ ወይስ ወደ ሌላ ክለብ ትቀላቀላለህ?
ምትኩ (ባብል) :- ነገሌ አርሲ ከፍተኛ ደረጃ እንዲደርስ ፍላጎቴ ነው እኔም በተሻለ መድረክ መቅረብ ነው ምፈልገው።
ዳጉ Sport :- አሁን ላይ የዝውውር ጥያቄ ቀርቦልሀል ወይ?
ምትኩ (ባብል) :- አዎ ! ከሶስት ክለቦች የዝውውር ጥያቄ ቀርበውልኛል
ዳጉ Sport :- አሁን ባለህ አቋም ከፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ጥያቄ ቀርቦልህ ያውቃል ?
ምትኩ (ባብል) :- አዎ ቀርቦልኝ ነበር
በ2011 የድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ የነበረው ዘላለም ሽፈራው (ሞሪኖ) ጋር ተነጋግረን በወቅቱ ከቡድኑ አሰልጣኙ በመሰናበቱ በምትኩ ዩሀንስ ሳህሌ በመተካቱ ዝውውሩ ሳይሳካልኝ ቀርቷል።
ሌላው ከፍተኛ ሊግ ከሚገኙ በተለያዩ ሲዝኖች የተሻሉ ክለቦች የዝውውር ጥያቄ ቢያቀርቡልኝም በቤተሰብ ምክንያት መፈረም አሌቻልኩም።
ዳጉ Sport :- ዝውውሩ በቤተሰብ ምክንያት አልተሳካም ብለሀኛልና በምን ምክንያት ነው ?
ምትኩ (ባብል) :- ያው ቤተሰቤን የማስተዳድረው እኔ በመሆኔ ከነገሌ አርሲ መራቁ ለቤተሰቤ አመቺ ባለመሆኑ ርቂ መውጣት አልቻልኩም ።
አሁን ላይ ግን ሁሉም ነገር ቀመስተካከሉ በየትኛውም ቦታ ህጄ መጫወት እችላለሁ።
ዳጉ Sport :- በመጨረሻ ማለት የምትፈልገው ካለህ እድሉ ልስጥህ
ምትኩ (ባብል) :- እኔ በዚህ ደረጃ ላይ እንድገኝ ትልቁን ድርሻ የሚወስዱትን ደጋፊዎቼን ከልብ ማመስገን እወዳለሁ እነሱ ለኔ የተለዩ ናቸው በቃ ለነሱ ቃላት ያጥረኛል። ሌላው ለነዚህ ትልቅ ድጋፍ ለሚሰጡኝ ደጋፊዎቼ ቤተሰቦቼ እና ጓደኞቼ በፕሪሚየር ሊጉ መድረክ በመገኘት ለመካስ እና የኔን ጉዞ ለማሳመር ጠንክሬ እሰራለሁ ።
ስለ ምትኩ (ባብል) በቅርበት ከሚያውቁት ለዳጉ ስፖርት የሰጡት የግል ሀሳባቸው ከብዙ በጥቂቱ ልናካፍላቹህ ወደድን።
1. ምትኩ (ባብል) ምርጥ ችሎታ ያለው ልጅ ሲሆን የሚመታቸው ሹቶች ለበረኛ ፈታኝ ናቸው ምቴ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ልናየው የሚገባ ጎበዝ ልጅ ነው። በርታ ባብል ሲል ገልፆታል።
2. ምትኩ ባብል ክብር የሚገባው ድንቅ የእግር ኳሱ ንጉሳችን ነው ሁሌም ክብር ለሱ ይገባዋል ለታዳጊዎችም ጥሩ ምሳሌ ለጓደኞቹ የተሻለ ብርታት የሚሆን የነገሌ አርሲ ኩራት ታማኝ አገልጋያችን ነው። ሁሌም የተሻለ ደረጃ እንዲደርስ ምኞታችን ነው ። በርታልን የኛ ጀግናችን ሲል ገልፆታል።
3. ምትኩ ባብል በቅርበት የምናውቀው ወንድማችን ነው ። ባብል ከኳሱ ባሻገር ሜዳላይም ሆነ ከሜዳ ውጭ ያለው መልካም ባህሪ ለብዙ ታዳጊዎች ምሳሌ መሆን የሚችል ወጣት ተጫዋች ነው። አሁን ላይ እያሳየ ባለው ብቃት ካለበት ሊግ በላይ መጫወት የሚችልበት ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው። መልካሙን ሁሉ እንመኝልሀለን በማለት ሀሳቡን አጋርቶናል።
4. ባብል ብዙ አገልግሎ ግን ትንሽ ክብር የተሰጠው ድንቅ ወጣት ተጫዋች ነው። አሁን ባለንበት ሁኔታ “ብዙ በተንጫጫ በሆነበት ” ሰአት እንኳን እሱጋ በተግባር ነው ለወጣቶች ምርጥ ምሳሌ መሆን ሚችል ተጫዋች ነው። እሱ ከዚህም በላይ ይገባዋል አቅሙ ይናገራል ሁሌም ወጥ የሆነ አቋም ነው ባብል ጋር ያለው ከዚህ የተሻለ ሊግ ላይ እንጠብቀዋልን ሲል ሀሳቡን አጋርቶናል።
5. የሀገራችን እግር ኳስ እንደዚህ አይነት ልጆች አለማየቱ ሁሌም ያስቆጨናል በፕሪሚየር ሊጉ ያሉ አሰልጣኞች እንደዚህ አይነት ጠንካራ ኳስ ተጫዋች ታች እየወረዱ አለማየታቸው ለሀገራችን እግር ኳስ እድገት ሌላው እንቅፋት ነው። ባብል ጠንካራና ታታሪ የፊት መስመር ተጫዋች ስለ መሆኑ እኛ እንመሰክራለን። ማለት የምፈልገው ፈጣሪ ይርዳህ ማለት እወዳለሁ ወንድሜ ባብል ሲል የተሰማውን ሀሳቡን አጋርቶናል።
ስለ ምትኩ (ባብል) የተሰጡትን ሀሳቦች ያጋራናቹህ ሲሆን ዳጉ Sport ለዚህ ኮከብ መልካም እድል ተመኘች አበቃን።
©️ ዳጉ Sport by Nuru Kadaba