
#የኢትዮጵያ_እግር_ኳስ_ፌዴሬሽን ለ 2014 አም የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ለማስተናገድ የሚፈልጉ ካሉ ጥያቄውን በደብዳቤ አሳወቀ።
✍ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስር ከሚደረጉ ውድድሮች ውስጥ አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር በወንድና በሴት ለሚደረገው የ 2014 አም ውድድር ለማዘጋጀት ፍላጎት ላላቸው በደብዳቤ ጥያቄ ያሳወቁ ሲሆን በ 2013 አም በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ አስተናጋጅነት መከናወኑ ይታወቃል። ፌዴሬሽኑ የዘንድሮውን ለማስተናገድ ለሚፈልጉ ክልሎች ጥያቄውን የላከ ሲሆን ውድድሩን ለማከናወን ሊሟላ የሚገባ መስፈርቶችን በዝርዝር ገልፅዋል።
ለማስተናገድ ሊሟሉ የሚገባቸው
1. በቂ የመወዳደሪያ ሜዳና የልምምድ ሜዳ ያለው
2. በቂ የመኝታ አገልግሎት እና የምግብ አቅርቦት ያለው
3. የተሟላ የፀጥታ ሁኔታን ማመቻቸት የሚችል
4. በቂ የሆነ የህክምና አገልግሎት መስጠት የሚችል
5. በቂና የማይቋረጥ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ያለው
6. በአጠቃላይ በሁሉም በቂ መስተንግዶ ለማድረግ ፍቃደኛ የሆነ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሊሟሉ የሚገባቸው ዝርዝር መስፈርቶችን በማቅረብ አሳውቋል።
✅ በ 2013 አም የውድድር አመት የሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ውድድሩን በሚገባ እንግዶቿን አስተናግዳና ከበቂ በላይ ሜዳዎችን በማቅረብ ውድድሩ በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቋ አይዘነጋም። የወንድሮ አስተናጋጅ ሁኖ የሚመረጥ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ የተሻለ ልምድ በመውሰድ የተሳካ ውድድር እንዲያስተናግዱ #ዳጉ_Sport ምኞቷል ለመግለፅ ትወዳለች።
✍ ለበለጠ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን T.me/Dagu_Sport ይቀላቀሉ።
©️ ዳጉ Sport by Nuru Kadaba