AFCON2021 የፍፃሜ ጨዋታዎች ዳሰሳ
በካሜሮን አስተናጋጅነት ከጥር 1/2014 ጀምሮ ሲደረግ የነበረው የአፍሪካ ዋንጫ በሴኔጋል አሸናፊነት ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ ለደረጃ የተደረገውን ጨዋታ ደገሞ ካሜሮን አሸንፋለች፡፡ እንዚህን ጨዋታዎች እና አጠቃላይ ውድድሩን የምንዳስስበት የመጨረሻ ፅሁፋችን ነው

የፍፃሜ እለት ይደረጋል ተብሎ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የካሜሮንና ቡርኪናፋሶ የደረጃ ጨዋታ በአንድ ቀን ቀረብ ብሎ ከግማሽ ፍፃሜው ጨዋታ ብዙም እረፍትና ማገገም ሳይኖረው ነበር የተደረገው፡፡ ለዚህም ይመስል ነበር ካሜሮኖች ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪያቸውን ቪንሰንት አቡበከርን መጠባበቂያ ወንበር ላይ አስቀምጠው ጨዋታውን የጀመሩት፡፡ሁለቱ ቡድኖች በውድድሩ ጅማሮ አንድ ምድብ ላይ ሆነው የመክፈቻ ጨዋታ ያደረጉ እንደሆነ የሚታሰብ ሲሆን በፍፃሜውም ጨዋታ ይገናኙና የመዝጊያ ጨዋታ ይሀናል የሚለውን ግምት ሳያሳኩ ቀርተው ነው ከመዝጊያ በፊት በሚደረግ የደረጃ ጨዋታ የተገናኙት፡፡ በመጀመርያ የምድብ ጨዋታቸው አዘጋጇን ካሜሮንን በሜዳዋና በህዝቧ ፊት በአንድ ጎል ስትመራ ቆይታ ቆይታ ሁለት ጎል ተቆጥሮባት ሁለት ለአንድ የተሸነፈችው ቡርኪና ፋሶ ምናልባት ይህ የመበቀያ እድሏ እንደሚሆን ተገምቶ ነበር፡፡ እስከ 72ኛ ደቂቃው ድረስ የነበረው የጨዋታ ሂደትም ይህንን የሚመሰከር ሀቅ መስሎ ነበር፡፡ ቡርኪና ፋሶዎች በምድብ ጨወታቸው ካሜሮን ላይ ባስቆጠሩት አይነት የጨዋታ እንቅስቃሴ በተከላካያቸው ስቲቭ ያጎ አማካኝነት በ24ኛው ደቂቃ የመጀመርያ ጎል አስቆጠሩ፡፡ ከግብፁ የግማሽ ፍፃሜ ሽንፈት ስነልቦና ምንም ያላገገሙ የሚመስሉት ካሜሮኖች ምንም አይነት ምላሽ የመስጠት ፍላጎት አላሳዩም፡፡ ይባስ ብሎ በ43ኛው ደቂቃ ላይ በቀኝ የጎል መስመር በኩል ሌላኛው ወጣቱ የማችስተር ሲቲው በውሰት ለፈረንሳዩ ኢ.ኤስ ትሮየስ የሚጫወተው ተከላካካይ ኢሳ ካቦሬ ኳሷን ከመውጣት ታድጎ ያሻገራትን ግብ ጠባቂው አንድሬ ኦናና በራሱ ግብ ላይ አስቆጠራት፡፡ የመጀመርያው አጋማሽ በቡርኪናፋሶ 2 ለ 0 መሪነት ተጠናቆ ወደ መልበሻ ክፍለ ገቡ፡፡ አብዛኛው ተመልካች ውጤቱ በቡረኪናፋሶ አሻናፊነት እንደሚጠናቀቅ እምነት አሳደረ፡፡ የዚህ ማረጋገጫ ደግሞ ካሜሮኖች የቁርጥ ቀን ልጃቸው ቪንሰንት አቡበከርን ከእረፍት መልስ ቀይረው አስገብተው የነበር ቢሆንም በ49ኛው ደቂቃ አጥቂው ጅበሪል ኦታራ ከትራኦሬ የተሸገረለትን ኳስ አስቆጥሮ ውጤቱን ወደ 3ለ0 ማድረጉ ለካሜሮናውያን የበለጠ ተስፋ አስቆራጭ ሆነ፡፡ ይህ ግን እስከ 72ኛ ደቂቃ ነበር የቆየው፡፡ ካሜሮናውያን ተስፋቸው ማቆጥቆጥ የጀመረበትን ጎሎ በአጥቂያቸው ስቴፈን ባሆኮን አማካኝነት አስቆጠሩ፡፡ ጨዋታው 3ለ1 ሆነ፡፡ ሰዓቱ ግን በቂ አልነበረም፡፡ ልክ 85ኛ ደቂቃ ላይ ልማደኛወ አጥቂ ቪንሰንት አቡበከር ጎል አስቆጥሮ ውጤቱ ምናለባት ሊገለበጥ እንደሚችል የመጨረሻ ተስፋ ሰጠ፡፡ ይህም አልቀረም 87ኛው ደቂቃ ላይ አሁንም ቪንሰንት አቡበከር አቻ ምታደረገውን ጎል አስቆጥሮ የቸዋታው ታሪክ ተቀየረ፡፡ ሙሉ 90 ደቂቃው 3ለ3 በሆነ ውጤት ተጠናቆ ወደ መለያ ምቶች አመራ፡፡ በመለያ ምቱም ካሜሮን 5ለ3 በሆነ ውጤት የ3ኛት ደረጃ ጨዋታውን በአሸናፊነት አጠናቀቀች፡፡ ለካሜሮናውያን ጣፋጭ ድል ለተመልካች በስሜት ውጣውረድ የተሞላ አና አዝናኝ ጨዋታ ነበር፡፡ ቪንስንት አቡበከር በውድድሩ ያስቆጠራቸውን ጎሎች 8 አድርሶ ከፈረንጆቹ 1974 የግብፁ የአፍሪካ ዋንጫ ወዲህ በመድረኩ በዙ ጎሎች ያሰቆጠረ ተጫዋች ሆኗል፡፡በቀድሞ ስሟ ዛየር በአሁኑ ዲ.ሪ. ኮንጎ ባሸነፈችበት በዚህ ውድድር ዳዬ ሙላምባ የተባለ ተጫዋቿ 9 ጎሎች ነበር ያስቆጠረው፡፡
በተጠባቂው የግብፅና ሴኔጋል የፍፃሜ ጨዋታ ብዙ ክስተቶች የተስተዋሉበት ሲሆን በጨዋታው በ7ኛ ደቂቃ ላይ የተሰጠውን ፍፁም ቅጣት ምት የመድረኩ ክስተት ነበረው የግብፁ ግብ ጠባቂ ጋባስኪ የሳዲዮ ማኔን ምት አድኗል፡፡ የሊቨርፑል የቡድን አጋሩ ሞ ሳላህ ለጋባስኪ የሳዲዮ ማኒን ቴክኒክ በሚናገርበት ወቅት ሳዲዮ ማኒ ወደ ሁለት ቀርቦ ውይይታቸውን የተሳተፈበር ሂደት አነጋጋሪ ነበር፡፡ የሞሳላህ ምክር ሰርቶ ግብፅ ጎል ሳይቆጠርባ 120 ደቂቃዎ እንድትቆይ አድጎ ነበር፡፡ ግብፆች በግብ ጠባቂያቸው ፍፁም ቅጣት የማዳን አቅም በመተማመን ሴኒጋሎችም በቼልሲው በወቅቱ የፊፋ ኮከብ ግብ ጠባቂ በመተማመን ወደ መለያ ምት ባመሩት ጨዋታ ያልተጠበው ሆኖ ግብፆች በአብዱልሞኔም እና በላሼን አማካኝነት ሁለት ስተው ሴኔጋሎች ደገሞ በሳር አማካኝነት አንድ ብቻ ስተው የሁለቱ ሀያላን ፍልሚያ በሴኔጋል በመለያ ምት 4ለ2 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡ ይህንን ተከትሎ ሴኔጋል በታሪኳ ለመጀመርያ ጊዜ የአፍሪካን ዋንጫ በልታ ዋንጫ ከበሉ 15 ሀገራ መዝገብ ላይ ስሟን አስፍራለች፡፡ ለተከታታይ 8 አመታት በአሰልጣኝነት የአፍሪካ ዋንጫውን ትኩርት አድርጎ የሰራው የቀድሞ ተጫዋቿ የአሁኑ አሰልጣኝ አሊዩ ሲሴ ትኩረት ያገኘ ግለሰብ ሆኖ አምሽቷል፡፡ በውድድሩ ፍፃሜ ግብፆች እንባቸውን መቆጣጠር እስኪያቅታቸው ያነቡ ሲሁን በተቃራኒው ሴኔጋሎች የሚያደርጉትን እስካማያውቁ ድረስ በደስታ ሲፈነጥዙ አምሽተዋል፡፡በዚህ ጨዋታ የግብፁ ግብ ጠባቂ ጋባስኪ የማኔን ፍጹም ቅጣት ምት ጨምሮ በርካታ ጎል ሊሆኑ የሚችሉ ኳሶችን በማዳኑ የጨዋታው ኮከብ ተብሏል፡፡
በውድድሩ
- ቪነስንት አቡበከር ኮከብ ጎል አግቢ
- ሳዲዮ ማኔ ኮከብ ተጫዋች
- ሜንዲ ኮከብ ግብ ጠባቂ
በመባል ሽልማታቸውን ወስደዋል፡፡
©️ ዳጉ Sport by ወሰን ጴጥሮስ