AFCON 2021 Cameroon የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዳሰሳ

ሁለት ጨዋታች በቀሩት የካሜሮኑ የአፍካ ዋንጫ በአስገራሚነቱ እንደቀጠለ ሲሆን ረቡዕ እና ሀሙስ የተደረጉ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ውድድሩ ምን ያህል ጠንካራ፣ አዝናኝና እና ትኩረት ሳቢ እንደነበር ምስክር ነው፡፡
ረቡዕ እለት በስቴድ አህማዱ አህዲጆ ሰታድየም በኢትዮጲያዊው ዳኛ በአምላክ ተሰማ የተመራው የቡርኪና ፋሶ እና ሴኔጋል የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በሴኔጋል 3ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ጨዋታውን በድል ከተወጡት ከሴኔጋል ኳክብት ባልተናነሰ የእለቱ ዳኛ ያሳዩት ብቃት በተለያዩ አለም አቀፍ ሚዲያዎች እና በስፖርት ቤተሰቡ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ የጨዋታው ፍክክር የሀይል ሚዛን ያደላበትና ግጭቶች የበዙበት ቢሆንም በተረጋጋ እና በስክነት ውሳኔዎችን ሲወስኑ የነበሩት በአምላክ ተሰማ ሁለት አሳሰሳች የነበሩ የፍፁም ቅጣት ምት ይገባኛሎችን በቫር በመታገዝ ሳይሰጡ ቀርተዋል፡፡ እንደተጠበቀው የግጭትና የጉልበት ትንቅንቁ ያየለበት ጨዋታ የመጀመርያ አጋማሽ ያለምንም ጎል ቢጠናቀቅም በሁለተኛው አጋማሽ ሴኔጋሎች በ70ኛ እና 76ኛ ደቂቃዎች ላይ የፒ.ኤስ.ጂው አብዱ ዲያሎ እና የአሎምፒክ ማረሴው ባምባ ዲዬንግ አከታትለው ባስቆጠሩት ጎል ሁለት ለምንም መምራት ቻሉ፡፡ ቡርኪናፋሶዎች ተስፋ ባለመቁረጥ ወደጨዋታ የመመለስ ጥረታቸው ተሳክቶላቸው በ82ኛ ደቂቃ ላይ በብላቲ ቱሬ አማካኝነት ጎል አግብተው የአቻነት ጎል ፍለጋ መሯሯጥ ጀመሩ፡፡ ነገር ግን ይህ ተስፋቸው የቆየው ለ5 ደቂቃዎች ያህል ብቻ ነበር፡፡ ሴኔጋሎች በ87ኛ ደቂቃ ላይ በሊቨርፑሉ ኮከባቸው በሳይዶ ማኔ አማካኝነት ጎል አስቆጥረው ጨዋታው 3ለ1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡ ሳድዮ ማኒ በውድድሩ ያስቆጠራቸው ጎሎች ብዛ ሶስት ሆነውለታል፡፡ውጤቱን ተከትሎ ቡርኪና ፋሶዎች ቅዳሜ ለደረጃ ሲጫወቱ ሴኔጋች እቅዳቸው ተሳክቶ እሁድ ጥር 29 ለፍፃሜ ለዋንጫ ይጫወታሉ፡፡

የቀጣዩ ቀን ተናፋቂው የአዘጋጇ ካሜሮንና የግብፅ ጨዋታ ነበር፡፡ ከመጀመሩ በፊት ውጤቱን ለመገመት አስቸጋሪ የነበረው ይህ ጨዋታ እንደግምቱ ሁሉ120 ደቂቃዎችን ያለምንም ጎል ነው የተጠናቀቀወ፡፡ አሸናፊውን ለመለየት ከተሰጡትን አምስት አምስት መለያ ምቶች ውስጥ በኮትዲቯሩ ጨዋታ የኤሪክ ቤይሊን ምት አድኖ ግብፅን ያሳለፋት ከሞሮኮው ጨዋታ ጉዳት ብዙም ሳያገግም የሀገር ፍቅር አስገድዶት ወደ ጨዋታ የገባው ግብ ጠባቂው መሀመድ ቆትብ አቡ ጋባል ጋባስኪ የካሜሮኖቹን የሞኩንዲን፣ ሊያ ሲሊኪና ጂዬን ምቶች አድኖ ግብፅ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋ ለዋንጫው ጨዋታ እንድታልፍ አድርጓታል፡፡ ጨዋታው በብዙ ቁጥር የካሜሮኖች የበላይነት የነበረው ቢሆንም የግብፆች አልሸነፍባይነት ለብዙ ሀገር ተጫዋቾች እንደሞዴል የሚጠቀስ ሆኖ አልፏል፡፡

ለደረጃ በሚደረግ የቅዳሜ ጨዋታ ከኢትዮጲያ ጋር በምድብ ድልድሉ የነበሩት ካሜሩንና ቡርኪና ፋሶ የሚገናኙ ሲሆን በምድብ ጨዋታቸው ካሜሮኖች ከመመራ ተነስተው በቪንሰንት አቡበከር ሁለት ጎሎች 2ለ1 ማሸነፋቸው ይታወቃል፡፡
እሁድ በሚደረግ የፍፃሜ ጨዋታ አለም በጉጉት እንዲጠብቀው ባደረገው ክስተት ሁለቱ የሊቨርፑል ኳክብት ሞ ሳላህ እና ማኔ በተቃራኒ የሚገናኙበት የግብፅ እና የሴኔጋል ጨዋታ ጥሩ ፉክክር እንደሚታይበት የሚገመት ሲሆን የቡድን ጓደኛማቾቹ ለሀገራቸው የሚያደርጉት አስተዋፅኦም የሚለካበት ይሆናል፡፡

ሴኔጋል ለፍፃሜ የደረሰቸው
በምድብ ቢ ጨዋታ ዚምባብዌን 1ለ0 አሸንፋ፣ ከጊኒና ማላዊ አቻ ውጥታ በ5 ነጥብ 1ኛ ሆና ከምድብ አልፋ፣ በ16 ውስጥ ጨዋታ ኬፕ ቨርዴን 2ለ0 አሸንፋ፣ በሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ኢኳቶሪያል ጊኒን 3ለ1 አሸንፋ እና በግማሽ ፍፃሜው ጨዋታ ቡርኪና ፋሶን 3ለ1 አሸንፋ ነው፡፡
ግብፅ ልፍፃሜ የደረሰችው
በምድብ ዲ ጨዋታ በናይጄርያን 1ለ0 ተሸንፋ፣ ጊኒቢሳኦንና ሱዳንን በተመሳሳይ 1ለ0 አሸንፋ በ6 ነጥብ 2ኛ ሆና ከምድብ አልፋ፣ በ16 ውስጥ ጨዋታ አይቮሪኮስትን በመለያ ምቶች አሸንፋ፣ በሩብ ፍፃማ ጨዋታ ሞሮኮን 2ለ1 አሸንፋ እና በግማሽ ፍፃሜው ጨዋታ ካሜሩንን በመለያ ምቶች አሸንፋ ነው፡፡
©️ ዳጉ Sport