AFCON 2021 የአፍሪካ ዋንጫ
የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዳሰሳ

ጥር 1 ተጀምሮ
ወደ መገባደጃው የደረሰው የአፍካ ዋንጫ 20 ሀገራትን አሰናብቶ 4 ሀገራትና 4 ጨዋታዎች ብቻ ቀርተውታል፡፡ እንዚህም ለፍፃሜ የሚደረጉ
ሁለት ጨዋታዎች፣ ለደረጃ የሚደረግ አንድ ጨዋታ እና ለዋንጫ የሚደረግ አንድ ጨዋታ ናቸው፡፡ ለዚህ ክብር የበቁ ሀገራትም ቀድሞ
በኢትዮጵያ ምድብ የሚገኙት ሁለቱ ሀገራት አዘጋጇ ካሜሮንና ቡርኪና ፋሶ፣ እንዲሁም የሊቨርፑሎቹ ክዋክብት የያዙት ግብፅና ሴኔጋል
ናቸው፡፡ እንዚህ ሀገራት የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎቻቸው ምን ይመስል እንደነበር እንመልከት
ካሜሮን በቶኮ
ኢካመቢ የ50ኛ እና 57ኛ ደቂቃዎች ጎል አስገራሚዋን ጋምቢያ ጉዞዋን የገታችበትን የ2 ለ 0 ድል አሳክታ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ተቀላቅላለች፡፡
ቶኮ ኢካመቢ በመድረኩ ያስቆጠራቸውን የጎሎች ብዛት ወደ አምስት አሸጋግሮ 6 ጎሎች ካሉት የቡድን አጋሩ ቪንሰንት አቡበከር ጋር
ለኮከብ ጎል አግቢነት ይፎካከራል፡፡
ቡርኪናፋሶ የሰሜን
አፍሪካዋን የአረብ ሀገር ቱኒዚያን በ45+3ኛ ደቂቃ ላይ በኦውታራ አማካኝነት ባስቆጠረችው በቸኛ ጎል 1 ለ 0 አሸንፋ ግማሽ ፍፃሜውን
የተቀላቀለች ሁለተኛዋ ሀገር ናት፡፡ ጎል አስቆጣሪው አውታራ በ82ኛ ደቂቃ ላይ ከሜዳ በቀይ ካርድ ቢወገድም ቱኒዚያዎች ወደ ጨዋታው
ተመልሰው ጎል ማቆጠር ሳይችሉ ጨዋታው ተጠናቋል፡፡
አስገራሚ ፉክክር
ይታይበታል ተብሎ የተጠበቀው የግብፅና የሞሮኮ ጨዋታ እንደተጠበቀው ሆኖ ከ120 ደቂቃዎች ፍልሚያ በኋላ በግብፅ የ2ለ1 አሸናፊት
ተጠናቋል፡፡ ሞሮኮዎች በፍፁም ቅጣት ምት ጨዋታው ከተጀመረ ገና በ6ኛ ደቂቃ ላይ በሲፊያን ቦውፋል አማካኝነት ጎል አስቆጥረው የቸዋታውን
የአሸናፊነት ግምት ወስደው የነበር ቢሆንም በስነልቦና ጠንካራ የነበሩት ግብፆች ከእረፍት መልስ በ53ኛ ደቂቃ በኮከባቸው ሞሀመድ
ሳላህ አማካኝነት ባስቆጠሩት ጎል አቻ ሆነው ጨዋታው ተጨማሪ 30 የመፎካከረያ ደቂቃዎች እንዲኖሩት አደረጉ፡፡ከእረፍት መልስ ተከላካዩን
ሂጋዚይን ቀይሮ ገብቶ የነበረው አማከዩ ትሬዜጌትልክ በ100ኛ ደቂቃ ላይ በአስደናቂ ብስለት ከሳላህ የተሻገረለትን ኳስ በጥሩ አጨራረስ
አስቆጥሮ ግብፆችን አሸናፊ አድርጓል፡፡ በጫወታው ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ መጎሻሸሞች የነበሩት ቢሆንም ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ
የግብፅ ተጫዋቾች የሞሮኮን ተጫዋቾች ያፅናኑበት መንገድ አነጋጋሪ ሆኖ ነበር፡፡
ሴኔጋል ምህረት
የለሽ መሆኗን አሳይታ ግማሽ ፍፃሜውን በተቀላቀለችበት የመጨረሻ ጨዋታ ኢኳቶሪያል ጊኒን 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡ ሴኒጋሎች
በ28ኛ ደቂቃ ላይ ከሳዲዮ ማኒ የተሸገረለትን ኳስ አጥቂው ዳይዲዩ አስቆጠሮ መሪ መሆን ቢችሉም ኢኳቶሪያል ጊኒዎች ከእረፍት መልስ
በቡይላ አማካኝነት በ57ኛ ደቂቃ ላይ ጎል አስቆጥረው አቻ ሆነው ወድ ጨዋታው ለመመለስ ሞክረው ነበር፡፡ ምህረት የለሾቹ ኩያቴና
ሳር በ68ኛ እና 79ኛ ደቂቃዎ ላይ ባስቆጠሩት ተከታታይ 2 ጎሎች ሴኔጋሎች 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈው ግማሽ ፍፃማን ተቀላቅለዋ፡፡
በግማሽ ፍፃሜ
ጨዋታዎች ቡርኪናፋሶ እና ሴኔጋል እንዲሁም ግብፅ እና አዘጋጇ ካሜሩን
የሚፋለሙ ይሆናል፡፡
የግማሽ ፍፃሜ ጫዋታ
የግማሽ ፍፃሜ
ጨዋታዎች
Ø ቡርኪና ፋሶ ከ ሴኔጋል
ሮብ ምሽት 4፡00
ሰዓት
Ø ካሜሩን ከ ግብፅ
ሀሙስ ምሽት 4፡00 ሰዓት
©️ ዳጉ Sport by Wosen ፔጥሮስ