በአርባምንጭ ከተማ ለሚካሄደው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ወደ ከተማዋ ለተጓዙ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል ተደረገ።

የአርባ ምንጭ ከተማ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምክትል ከንቲባ አቶ ደረጄ ጳውሎስ፣ የከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ሰይድ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ም/ዋና ፀሐፊ እና የጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴ ጥሪ የተደረገላቸው የከተማና የዞን አመራሮች በዛሬው እለት ወደ ከተማዋ ለገቡት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኘሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ ዋና ፀሐፊ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ፣ የጉባኤው አባላት፣ ዳሬክተሮችና ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች በአርባምንጭ ከተማ አየር ማረፊያ አቀባበል ተደርጓላቸዋል።
ለጉባኤው ዝግጅት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ አባላት ወደ አርባምንጭ ከተማ ከሁለት ቀናት በፊት በመገኘት የቅድመ ዝግጅት ሥራውን ከአርባምንጭ ከተማ የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ጋር በጋራ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ታህሳስ 23 – 24 / 2014 ዓ.ም ሲምፖዚየም እና ጠቅላላ ጉባኤው ይካሄዳል።
Via #EFF
JOIN T.me/Dagu_Sport